top of page

ሰለስቱ ፤ ወደራስ ጉዞ


ተመክሬ ነበር ፣ ስኬት እንድሰፍር ወዳጅ እንዳኮራ ፣ ጠላት እንዳሳፍር የህይወቴን እርሻ ፣ ላዳብር ላለማ እሰው ዘንድ ስፈትሽ ከዐለም ጓዳ ስሻ ከእንደኔው ሰባራ የፈራጅ ደንባራ

ስኳትን ከርሜ ፣ ውስጥ እግሬ ቢደማ ባጣው ውስጤ ገባሁ መሄጃ ቢጠፋኝ፣ ከኔው ጋር ተግባባሁ፧ ይዤው መባከኔን ልቤ መች አወቀ ፍፁምነት ዕንቊው፣ ማንም በማይዘርፈው ሹፈትን በናቀ፣ ሓሴታዊ አልማዝ እንዳሸበረቀ እውስጤ አገኘሁት፣ እጉድለቴ መሀል እንደተደበቀ።

Commentaires


bottom of page